Home › Groups › Commercial Bank of Ethiopia - Official
Commercial Bank of Ethiopia - Official Telegram
Telegram Channel Link

Commercial Bank of Ethiopia - Official Telegram Channel Link

★★★★★ 0.0 (0 ratings)
👁 1 views ↗ 0 joins
🌐 International 🌐 English # Business, Advertising & Marketing
About this telegram channel link
Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with 1,971 branches and service outlet across the country. @ www.facebook.com/combanketh @ www.twitter.com/combankethiopia
Telegram Channel

Latest public posts from this Telegram channel.

200 subscribers
31 Oct 2026 latest post
Click to fetch the latest posts directly from Telegram.
Telegram post media የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር ያለውን የረጅም ዓመታት አጋርነት በማጠናከር የግሩፑን የልማት ፕሮጀክቶች በፋይናንስ ከማገዝ ባለፈ፣ ከግሩፑ ጎን በጽናት እንደሚቆም የባንካችን ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ አረጋገጡ።

ሁለቱ ተቋማት በአጋርነታቸው ሊያጠናክሯቸው በሚችሉ የትብብር መስኮችና የጋራ የልማት ዕድሎች ላይ ተወያይተዋል።
=======================
በውይይቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ፣ ባንካችን ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ የተለያዩ ኩባንያዎቹ እንዲስፋፉና የሥራ እንቅስቃሴያቸውን እንዲያሳድጉ የጎላ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸዋል።

ባንካችን ከግሉ ዘርፍ ጋር በሚያደርገው የፋይናንስ ትብብር የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እድገት ለማፋጠን እና ምርታማ ኢንቨስትመንቶችን ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነትም አረጋግጠዋል።

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በፋይናንስ ዘርፍ ያለውን ትልቅ ሚና አድንቀው፣ ባንኩ ለግሩፑ የእድገትና የመስፋፋት ጉዞ እያደረገ ባለው ድጋፍ አመስግነዋል።

45 ኩባንያዎችን ያቀፈውና በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የተሰማራው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ በርካታ የልማት ሥራዎችን በማከናወን ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦም አንስተዋል።

በተለይም በከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ እየተገነባ ለሚገኘው የሞሃመዲያ ቪሌጅ ፕሮጀክትና ለሌሎች የግሩፑ የልማት ውጥኖች የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ ባንካችን ያለውን ዝግጁነት በውይይቱ ላይ አረጋግጧል።

አቶ አቤ ሳኖ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በ2018 ዓ.ም. ለሀገሪቱ 31 ቢሊዮን ብር ግብር መክፈሉን በማድነቅ፣ ግሩፑ በኢንቨስትመንት፣ በሀብት ፈጠራና በሀገራዊ ልማት ላይ እያበረከተ ያለውን ወሳኝ አስተዋጽኦ አድንቀዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እድገትና ለሀገራዊ ልማት አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ፕሮጀክቶችን በፋይናንስ በመደገፍ ከግሩፑ ጎን በጽናት እንደሚቆም ፕሬዝዳንቱ አረጋግጠዋል።

የሀገር ዋልታ የሆኑት ሁለቱ ተቋማት፤ በጋራ አጋርነት፣ በጠንካራ ትብብርና በተቀናጀ ጥረት የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እድገት ለማፋጠን የጀመሩትን ጉዞ ይበልጥ አጠናክረው ይቀጥላሉ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
Telegram post media በሀሰተኛ የክፍያ መግለጫ እንዳይጭበረበሩ መላ ዘይደናል!
**************

 
በሲቢኢ ሞባይል ባንኪንግ ክፍያ ሲቀበሉ ከፋዩ ሞባይሉ ላይ የሚያሳይዎትን  የክፍያ መግለጫ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ይህን ያድርጉ፡
 
👉 የክፍያ መግለጫው ላይ የሚገኘው የ 'ራይት' ምልክት ☑️ የሚንቀሳቀስ መሆኑን ልብ ይበሉ፤

👉 የከፋዩ ሞባይል ላይ የሚታየውን የክፍያ መግለጫ ሲነኩት ‘PAID’ የሚል ጽሁፍ እንደሚወጣ ያረጋግጡ።
 
********

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
 
#cbe #digitalbanking #digitalethiopia #mobilebanking
ከሀገርዎ ጋር ኮኔክት ያድርጉ፤
ወዳጅ ዘመዶችዎን ያስደስቱ!
 
CBE Connect

**********

በውጭ ሀገር በቀላሉ የሲቢኢ ኮኔክት ዲጂታል ዋሌት ተጠቃሚ በመሆን
በነፃ፣ በፍጥነት፣ ዳጎስ ካለ ጉርሻ ጋር ቀጥታ ወደ ባንክ ሂሳብ ገንዘብ  ልከው የወዳጅ ዘመዶችዎን ምርቃት ይቀበሉ!

አሁኑኑ መተግበሪያውን ስልክዎ ላይ በመጫን የሲቢኢ ኮኔክት ዋሌት ባለቤት ይሁኑ!
 
⬇️ ለአንድሮይድ -
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.connectethiopia&hl=en

⬇️ ለአይፎን - https://apps.apple.com/us/app/cbe-connect/id6753888802

*********
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

#CBE #CBEconnect #DigitalWallet #EthiopiaDiaspora
Telegram post media በጣናው ደርቢ ማን ያሸንፋል?
*********
በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2019 ዛሬ
አፄዎቹ ከጣና ሞገዶቹ በባህር ዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም ከቀኑ 9፡00 ይፋለማሉ።
 
በሌላ ተጠባቂ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ከአዳማ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ 9፡00 ይገናኛሉ!
 
ትኬትዎን በሲቢኢ ብር ፕላስ ባሉበት ይቁረጡ፤
ጨዋታውን በስታዲየም ከነድባቡ ይመልከቱ!
 
⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️
 
ትኬትዎን ባሉበት በሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ ለመቁረጥ እንዲህ ያድርጉ፡
 
⚽️ የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ ላይ ወደሚገኘው ‘ሚኒ አፕስ’/ ‘Mini Apps’ ይግቡ፣
⚽️ ‘Ethio Sport’ የሚለውን ሚኒ አፕ ይክፈቱ፣
⚽️  ሊመለከቱ የፈለጉትን ጨዋታ ይምረጡ፣
⚽️  ሊቀመጡበት የፈለጉትን የስታዲየም ቦታ ይምረጡ፣
⚽️  የትኬት ብዛት ይወስኑና ‘Next’ የሚለውን ይጫኑ፣
⚽️ ስም እና ባለ 16 አሀዝ የፋይዳ ቁጥር ያስገቡ፣
⚽️ ‘Pay with CBE Birr’ የሚለውን ይጫኑ፣
⚽️ የሚስጥር ቁጥርዎን በማስገባት ክፍያዎን ያጠናቁ፣
⚽️ ክፍያው በተሳካ ሁኔታ ሲፈጸም የሚደርስዎትን ዲጂታል ትኬት ስክሪን ሾት አድርገው ወይም አውርደው ይያዙና ወደስታዲየም ሲገቡ ያሳዩ።
 
***
የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያን ለማግኘት፡

• ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr

• ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787

*****
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

#cbe #PremierLeague #EthiopianPremierLeague #CBEEthiopianPremierLeague
Telegram post media በቀን እስከ 1 ሚሊዮን ብር ግብይት
በካርድዎ መፈፀም ይችላሉ!
***************
በግብይት እና በአገልግሎት መስጫ ስፍራዎች ጥሬ ገንዘብ መያዝ ሳይጠበቅብዎ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የክፍያ መፈፀሚያ ማሽኖች (ፖስ) በመጠቀም በቀን

👉 በመደበኛ ካርድዎ እስከ 500 ሺ ብር
👉 በጎልድ ካርድዎ እስከ 700 ሺ ብር
👉 በፕላቲኒየም ካርድዎ እስከ 1 ሚሊዮን ብር ግብይት መፈፀም ይችላሉ!

✅ ልብ ይበሉ፡

በካርድዎ ሲከፍሉ የፖስ ማሽኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሆኑን ያስተውሉ፤
የግብይት መጠኑ ሳይዘገይ ከሂሳብዎ ስለሚቀነስ፣ ቀሪ ሂሳብዎን በትክክል ያውቃሉ!

****
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

#cbe #digitalbanking #pos #banking #ethiopia
Telegram post media ተጨማሪ ጉርሻ ያግኙ!
***

ውድ ደንበኞቻችን፡

ከው
ጭ ሀገራት በ #EthioDirect ፣ #CBEConnect ፣ #CashGo ፣ #Botim ፣ #WegenSend ፣ #LakiRemit ፣ #EthioPay ፣ #ArifPay ፣ #DestaPay እና #MojoMoney ዲጂታል የገንዘብ መላኪያ መተግበሪያዎች ገንዘብ ሲላክልዎ በእለታዊ የውጭ ምንዛሬ የመሸጫ ተመን ላይ ተጨማሪ 7.875 በመቶ ጉርሻ፤ 

እንዲሁም ከባንካችን ጋር በሚሠሩ ዓለም አቀፍ የሐዋላ አስተላላፊዎች በኩል ገንዘብ ሲላክልዎ በእለታዊ የውጭ ምንዛሬ የመሸጫ ተመን ላይ ተጨማሪ 7.824 በመቶ  ጉርሻ የምናበረክትልዎ መሆኑን በደስታ እንገልፃለን!

****

 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
 ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

For more currency exchange rates:
https://combanketh.et/exchange-rates?srcPage=home

#exchangerate #CBE #commercialbankofethiopia #Birr #rate #currency #Ethiopia  combanketh.et
Telegram post media የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 3ኛውን የሳይበር ደህንነት ወር በማስመልከት ያዘጋጀው የሁለት ቀናት ጉባኤ እና አውደ ርዕይ በስኬት ተጠናቋል።
*************

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ “Don’t Make It Easy for Them! AI-Powered Defence. Zero Trust Mindset.” በሚል መሪ ቃል እያከበረ ከሚገኘው የሳይበር ደህንነት ወር ጋር በተገናኘ ያዘጋጀው የሁለት ቀናት ጉባኤ እና አውደ ርዕይ ተጠናቋል።

በሁለቱ ቀናት መርሀ ግብር ከሳይበር ደህንነት ጋር በተገናኙ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያጠነጠኑ የፓናል ውይይቶች ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገራት በተገኙ በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ ባለሙያዎች እና ምሁራን ተደርገዋል።

በመድረኩ ዓለማቀፍ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የሳይበር ደህንነትን የተመለከቱ ፅሑፎችም ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በውይይቱም ለሳይበር ደህንነት፣ ለመረጃ ጥበቃና ለዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም የሚሰጠው ትኩረት ከምንጊዜውም በላይ መጠናከር እንዳለበት ተጠቁሟል።

በተለይ የዲጂታል መንታፊዎችና አጭበርባሪዎች አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ (AI] እና ሌሎች ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ በመሆናቸው የፋይናንስ ተቋማት ዘመኑን በዋጀ መልኩ የሳይበር ደህንነታቸውን ይበልጥ አስተማማኝ እና ተዓማኒ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አፅንኦት ተሰጥቶበታል።

የባንካችን የሳይበር ደህንነት ስራዎችን የሚያስቃኝ እንዲሁም ጀማሪ እና ልምድ ያካበቱ ሀገር በቀል እና የውጭ ሀገራት የቴክኖሎጂ አቅራቢ ተቋማት (Fintechs) በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተደገፉ የሳይበር ደህንነትን መጠበቅ የሚያስችሉ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎቻቸውን ያቀረቡበት አውደ ርዕይ እንዲሁ የመርሐ ግብሩ አካል ነበር።

ከጉባኤው ውጤታማና አሳታፊ ውይይቶች እንዲሁም ከጎንዮሽ የልምድ ልውውጦች የሳይበር ደህንነት ግንዛቤን የሚያሳድጉ ግብዓቶች ተገኝተዋል።

በወጣት የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች መካከል በተደረገ ‘የሀኪንግ’ (Hacking) (Capture The Flag (CTF)) ውድድር ከአንድ እስከ ሶስት ለወጡ አሸናፊዎች በመርሐ ግብሩ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በማጠቃለያው የመርሐ ግብሩ ተባባሪ አዘጋጅ CIO Africa ን ጨምሮ በዝግጀቱ ላይ በአጋርነት፣ አውደ ርዕይ በማቅረብ፣ በፓናል ውይይት እና ጽሁፍ በማቅረብ፣ በዝግጅቱ ላይ በመታደም እንዲሁም መርሐ ግብሩን በተሳካ ሁኔታ በማካሄድ ለተሳተፉ አካላት በሙሉ ከባንካችን የኢንፎርሜሽን ሴኪውሪቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ተወካይ አቶ ዮሀንስ የማነ እና ከ CIO Africa መስራች እና ዳይሬክተር ሚስተር አንድሪው ካራንጃ ምስጋና ቀርቦላቸዋል።

*************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

#cbe #Cbe3rdcybersecurity #Cybersecurity #Cybersecurityawarenessmonth #zero_trust
Telegram Channel Link information
Country 🌐 International
Language English
Type Telegram Channel Link
Subscribers 200
Rate this group

How would you rate this community?

0.0 ★ Join Group →