Home › Groups › Bible study/ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ✝
Bible study/ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ✝ Telegram
Telegram Channel Link

Bible study/ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ✝ Telegram Channel Link

★★★★★ 0.0 (0 ratings)
👁 1 views ↗ 0 joins
🌐 International 🌐 English # Jobs & Career
About this telegram channel link
Daily Bread/የእለት እንጀራ
Telegram Channel

Latest public posts from this Telegram channel.

219 subscribers
19 May 2024 latest post
Click to fetch the latest posts directly from Telegram.
Telegram post media የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መንፈስ ቅዱስ ተሞሉ!

"...... በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥ ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው። እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው። በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር።"

የሐዋርያት ስራ 2:1-4

እዚህ ክፍል ላይ የምንመለከተው ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ በዓለ ኀምሳ በሚባለው ቀን በአንድነት እና በአንድ ልብ ሆነው ሳሉ መንፈስ ቅዱስ ተምሉ እንዲሁም በተለያየ ልሳን እንዲናገሩ መንፈስ ስለሰጣቸው በተለያየ ልሳን ይናገሩ ጀመር።

“እነሆም፥ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ።”
— ሉቃስ 24፥49

ደቀ መዛሙርቱ ጌታ የሰጣቸውን ትዕዛዝ ጠብቀው ስለቆዩ ቃል በገባላቸው መሰረት የመንፈስ ቅዱስን ኃይል እንዲቀበሉ እና እንዲሞሉ ጊዜውን ጠብቆ ወደ እነሱ መጣ። ዛሬም እኛ በመንፈስቅዱስ ኃይል ከእግዚአብሔር ምሪትን አየተቀበልን መንቀሳቀስ ይሁንልን።


እግዚአብሔር ይባርካችሁ!!!
Telegram post media የኢየሱስ ሐዋርያት ከ 12 መካከል አንዱ በነበረው በይሁዳ ፈንታ ደቀ መዝሙር መረጡ!



"... በዚህም ወራት ጴጥሮስ መቶ ሀያ በሚያህል በሰዎች ማኅበር አብረው በነበሩ በወንድሞቹ መካከል ተነሥቶ አለ።
ወንድሞች ሆይ፥ ኢየሱስን ለያዙት መሪ ስለሆናቸው ስለ ይሁዳ መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት አፍ የተናገረው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ይገባ ነበር፤
ከእኛ ጋር ተቈጥሮ ነበርና፥ ለዚህም አገልግሎት ታድሎ ነበርና። ይህም ሰው በዓመፅ ዋጋ መሬት ገዛ በግንባሩም ተደፍቶ ከመካከሉ ተሰነጠቀ አንጀቱም ሁሉ ተዘረገፈ፤ በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ሁሉ ታወቀ፤ ስለዚህም ያ መሬት በቋንቋቸው አኬልዳማ ተብሎ ተጠራ፥ እርሱም የደም መሬት ማለት ነው። በመዝሙር መጽሐፍ፦ መኖሪያው ምድረ በዳ ትሁን የሚኖርባትም አይኑር፤ ደግሞም፦ ሹመቱን ሌላ ይውሰዳት ተብሎ ተጽፎአልና። ስለዚህ ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ከእኛ ዘንድ እስካረገበት ቀን ድረስ፥ ጌታ ኢየሱስ በእኛ መካከል በገባበትና በወጣበት ዘመን ሁሉ ከእኛ ጋር አብረው ከነበሩት ሰዎች፥ ከእነዚህ አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር ይሆን ዘንድ ይገባል። ኢዮስጦስም የሚሉትን በርስያን የተባለውን ዮሴፍንና ማትያስን ሁለቱን አቆሙ። ሲጸልዩም፦ የሁሉን ልብ የምታውቅ አንተ ጌታ ሆይ፥ ይሁዳ ወደ ገዛ ራሱ ስፍራ ይሄድ ዘንድ በተዋት በዚህች አገልግሎትና ሐዋርያነት ስፍራን እንዲቀበል የመረጥኸውን ከእነዚህ ከሁለቱ አንዱን ሹመው አሉ። ዕጣም ተጣጣሉላቸው፥ ዕጣውም ለማትያስ ወደቀና ከአሥራ አንዱ ሐዋርያት ጋር ተቈጠረ።"

የሐዋርያት ስራ 1:15 - 26

እዚህ ክፍል ላይ እንደምንመለከተው ኢየሱስ ከመረጣቸው ሐዋርያት ብሎ ከሰየማቸው 12 ደቀመዛሙርት መካከል ኢየሱስን በ 30 ዲናር ሸጦ መሬት የገዛው ይሁዳ በገዛው መሬት ላይ በግንባሩ ተደፍቶ ስለሞተ በእርሱ ምትክ ሌላ ሐዋርያ ለመምረጥ እንደተነሱ እናያለን። ከኢየሱስ ጋር አብረው ሲጓዙ የነበሩት ደቀ መዛሙርት የእግዚአብሔርን ፈቃድ መከተል ያለውን ጥቅም ስለሚያውቁ፤ በመካከላቸው ከነበሩት ከሁለቱ እጬዎች እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እጣው የወደቀበት ቦታውን እንዲይዝ በማሰብ እጣ አወጡ። የእግዚአብሔር ፈቃድ የነበረበትም በቦታው ተተካ።
ከዚህ ክፍል የምንማራቸው ቁምነገሮች ቢኖሩ ገንዘብ ምንም አስፈላጊ ቢሆንም ከልክ በላይ የገንዘብ ፍቅር ግን ሕይወታችንን እንዲሁም ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን መልካም ግንኙነት ሊያሳጣን ይችላል። በዚህ ምክንያት ነው ይሁዳ ሕይወቱ በከንቱ ሞት የተቋጨው።

“ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።”

1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥10


እግዚአብሔር ይባርካችሁ!!!
Telegram post media የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በአንድነት ሆነው ይፀልዩ ነበር!

"...በዚያን ጊዜ ደብረ ዘይት ከሚባለው ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ እርሱም ከኢየሩሳሌም የሰንበት መንገድ ያህል የራቀ ነው።
በገቡም ጊዜ ወደሚኖሩበት ሰገነት ወጡ፥ ጴጥሮስና ዮሐንስም፥ ያዕቆብም፥ እንድርያስም፥ ፊልጶስም፥ ቶማስም፥ በርተሎሜዎስም፥ ማቴዎስም፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም፥ ቀናተኛ የሚባለው ስምዖንም፥ የያዕቆብ ልጅ ይሁዳም።
እነዚህ ሁሉ ከሴቶችና ከኢየሱስ እናት ከማርያም ከወንድሞቹም ጋር በአንድ ልብ ሆነው ለጸሎት ይተጉ ነበር።"

የሐዋርያት ሥራ 1: 12-14

እዚህ ክፍል ላይ እንደምንመለከተው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ ከእግሩ ስር ሲማሩ የነበሩት ሐዋርያትን እና የኢየሱስን እናት ቅድስት ማርያምን ጨምሮ ሌሎች ደቀ መዛሙርት ከጌታ በተቀበሉት ትዕዛዝ መሰረት በኢየሩሳሌም ሆነው በአንድነት ይፀልዩ ነበር።


"... እነሆም፥ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ።"

የሉቃስ ወንጌል 24:49

በተጨማሪም ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በነበረ ጊዜ በተደጋጋሚ ተግተው መፀለይ እንዳለባቸው ይናገር ነበር።
ዛሬም የእግዚአበሔር ቃል በእኛ ዘመን ይሰራል። እኛም ልክ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ያደርጉ እንደነበረው ዘወትር በፀሎት መትጋት አለብን። ይህንን ዘመን ማምለጥ የምንችለው ከእግዚአብሔር ጋር ስንሆን ነው። በግላችንመም በህብረትም ዘወትር የእግዚአብሔርን ፊት እንፈልግ። እግዚአብሔር ደግሞ ለሚፈልጉት የሚገኝ የቅርብ አምላክ ነው።

"... ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።"

ወደ ፊሊጵሲዩስ 4:6


እግዚአብሔር ይባርካችሁ!!!
Telegram post media ኢየሱስ ዳግም በክብር ይመጣል!

"...እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኵር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ፥ እነሆ፥ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ፤
ደግሞም። የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደስማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው።"

የሐዋርያት ሥራ 1 : 10-11

ኢየሱስ በምድር ላይ የመጣበትን ለሰው ልጆች የኃጢአት ስርየት ቤዛነት መሞትን ከፈፀመ በኋላ ወደ ሰማይ አርጓል። ጌታ ኢየሱስ በምድር ሳለ ለደቀ መዛሙርቱ እንደሚከተለው ብሏቸው ነበር።

"...በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤
ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ።"

የዮሐንስ ወንጌል 14 : 2-3

ኢየሱስ አሁንም በስራ ላይ ነው። ለወደደን ለእኛ ለልጆቹ ስፍራን ሊያዘጋጅ ነው ወደ አብ የሔደው። በቅርቡም ወደ ተዘጋጀልን ስፍራ ሊወስደን ይመጣል።
ጌታ በደጅ ነው። ተዘጋጅታችኋል? በኢየሱስ ክርስቶስ የምናምን የምስራቹን ቃል ላላመኑት የማድረስ ኃላፊነት አለብን። ወደ ኢየሱስ መምጣት እረፍት ነው። የከበደንን ቀንበራችንን ሊሸከምልን ዝግጁ ነው።

"...እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።"

የማቴዎስ ወንጌል 11 : 28



እግዚአብሔር ይባርካችሁ!!!
Telegram post media ኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሳኤ በኋላ ወደ ሰማይ አረገ!

የሐዋርያት ስራ 1:1-9
(ይህን ክፍል ከመጽሐፍ ቅዱስ እናንብብ)

እዚህ ክፍል ላይ እንደምናየው ኢየሱስ ከምት ከተነሳ በኋላ እስከሚያርግበት ቀን ድረስ ለደቀ መዛሙርቱ ይታይ ነበር። እርሱ ካረገ በኋላ ስለሚሆኑ ነገሮች እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጭምር ምን ማድረግ እንዳለባቸው ይነግራቸው ነበር። እርሱ እስኪሄድ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ እንደሚምሉ ጭምር ያስረዳቸው ነበር። መንፈስ ቅዱስን ከተሞሉ በኋላ በተለያየ የአለም ዳርቻ እየሄዱ ስለ እርሱ እንደሚመሰክሩ እየነገራቸው ጊዜው ደርሶ ስለነበር ወደ ሰማይ አረገ።

እንግዲህ ይህ ቃል የሚሰራው ለእኛም ጭምር ነው። ኢየሱስ ክርስቶስን የምንከተል ከሆነ የምስራች ቃል የሆነውን ወንጌል ለሰዎች የመናገር ኃላፊነት አለብን። ኢየሱስን ማገልገል እና ስለ እሱ መስበክ እንድንችል እግዚአብሔር ይርዳን።



እግዚአብሔር ይባርካችሁ!!!
Telegram post media የሐዋርያት ስራ !

ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የተፃፈው አገልጋይ እና ሀኪም በነበረው ሉቃስ ነው። ከሐዋርያት ስራ በተጨማሪ ከአፃፃፍ ዘዬው መረዳት እንደምንችለው የሉቃስ ወንጌልም የተፃፈው በተመሳሳይ ሰው ነው።
በፅሁፉ አጀማመር ላይ ተደራሽ የነበረው ቴዎፍሎስ የሚባል ሰው ቢሆንም እንደ አጠቃላይ ክርስቶስን ለሚከተሉ ጭምር ታስቦ የተፃፈ እንደሆነ የስነ መለኮት ተመራማሪዎች ያስረዳሉ።

የመጽሀፉ ክፍል እንደ አጠቃላይ ስለ መጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን አመሰራረት እና መስፋፋት ይተርክልናል። የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት እና ተከታዮች ለክርስትና መስፋፋት ያደረጉትን ታዛዥነትና አስተዋፅኦ እንመለከታለን።

ከዚህ በኋላ በተከታታይ የሐዋርያት ስራ መጽሐፍን እናጠናለን።

እግዚአብሔር ይባርካችሁ!!!
Telegram post media ካላየ የማያምነው ቶማስ!

" ኢየሱስም። ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለው።"

የዮሐንስ ወንጌል 20 : 29



እዚህ ምዕራፍ ከቁጥር 25 ጀምረን ስናነብ ከዚህ በፊት እንዳደረገው ደቀ መዛሙርቱ በር ዘግተው በተቀመጡበት ኢየሱስ በመካከላቸው መጣ። ከዚህ ቀደም ስላልነበረ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ ለሆነው ለቶማስ የጌታን መነሳት ሲነግሩት
ካላየ እና የተወጋ አካሉን ካልነካ እንደማያምን ስለተናገረ ኢየሱስ ካስነካው በኋላ እሱ አይቶ አመነ ነገር ግን ሳያዩ የሚያምኑ ብፁአን እንደሆኑ ተናገረ።

እኛም ዛሬ ኢየሱስን የምናምነው አይተነው ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ ስለገለጠልን ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1:15-16 ላይ እንዲህ ይላል:

"እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው። የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል።"



" ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ፤
ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል።"


የዮሐንስ ወንጌል 20 : 30- 31


እግዚአብሔር ይባርካችሁ!!!
Telegram post media ጌታችን ኢየሱስ ሞትን ድል አድርጎ ተነስቷል!

የዮሐንስ ወንጌል 20:11-25
(ይህንን ክፍል ከመጽሐፍ ቅዱስ አንብቡት)

ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት ከመቃብር ቦታ ወደ ቤታቸው ቢሄዱም ግን መግደላዊት ማርያም ግን እያለቀሰች እዛው ቀርታ ነበር። እያለቀሰች ወደ መቃብሩ ዞራ ስታይ ሁለት መላእክት በመቃብሩ ራስጌ እና ግርጌ ቆመው አየች። ለምን እንደምታለቅስ ሲጠይቋት ጌታዋን እንደወሰዱባትና ወዴት እንዳኖሩት እንደማታውቅ ነገረቻቸው እና ወደ ኋላ ዞር ስትል ኢየሱስ ቆሞ አየችው ነገር ግን የአትክልት ጠባቂ እንጂ ኢየሱስ አልመሰላትም ነበር። ምን እንደምትፈልግ ሲጠይቃት ጌታዋን እሱ ወስዶት ከሆነ የት እንዳደረገው እንዲነግራት ጠየቀችው። ኢየሱስም ማርያም ብሎ በስሟ ሲጠራት እሱ እንደሆነ አወቀች። ኢየሱስም ወደ ሌሎቹ ወንድሞች ሄዳ ወደ አባቱና አባታቸው እንዲሁም አምላኩ እና አምላካቸው እንደሚያርግ እንድትነግራቸው ባዘዛት መሰረት ሄዳ ለደቀ መዛሙርቱ ነገረቻቸው።
ያ ቀን በመሸ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ አይሁድን ፈርተው በር ዘግተው በተሰበሰቡበት ኢየሱስ መጥቶ በመካከላቸው ቆሞ ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው እና እጆቹንና ጎኑን አሳያቸው። ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ በመምጣቱ እጅግ ደስ አላቸው። ኢየሱስም አብ እንደላከው እነርሱንም እንደሚልካቸው ነግሯቸው እፍ ሲልባቸው መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ።


ኢየሱስ በፈራንበት እና በጨነቀን ሁኔታ ላይ ወደ ህይወታችን ገብቶ ነገርን መቀየር ይችላል። ያስጨነቃችሁ ነገር ካለ ኢየሱስ ጣልቃ እንዲገባዐፈቃድ ስጡት። ሞትን ድል አድርጎ የተነሳ ጌታ የሚሳነው ምንም ነገር አይኖርም።


"እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።"

1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5 : 7


እግዚአብሔር ይባርካችሁ!!!
Telegram post media ኢየሱስ ክርስቶስ ተቀብሮበት የነበረው መቃብር ባዶ ነው!

የዮሐንስ ወንጌል 20:1-10
(ይህንን ክፍል ከመጽሐፍ ቅዱስ አንብቡት)

የመቶ አለቃ ኒቆዲሞስ እና የአርማቲያስ ዮሴፍ ኢየሱስን ከሞተ በኋላ በአይሁድ ሰንበት (ቅዳሜ) ሊገባ ስለነበር ሬሳ መስቀል ላይ መሆን ስለሌለበት ከጲላጦስ ፈቃድ አግኝተው በተዘጋጀ አዲስ መቃብር ውስጥ እንደ ደንቡ ገንዘው ቀበሩት።
ሰንበት (ቅዳሜ) ካለፈ በኋላ እሁድ ከመንጋቱ በፊት ገና ጨለማው ሳይገፈፍ የኢየሱስ ተከታይ ከነበሩት ሴቶች አንዷ የሆነችው መግደላዊት ማርያም የኢየሱስን ሬሳ ለማየት ወደ መቃብር ሄደች። እዛ ስትደርስም መቃብሩ ላይ ተከድኖ የነበረው ድንጋይ ተፈንቅሎ አየች በዛ ላይ ኢየሱስ መቃብሩ ውስጥ አልነበረም። እየሮጠችም ሄዳ ሁኔታውን ለጴጥሮስ እና ጌታ ይወደው ለነበረው ደቀ መዝሙር (ዮሐንስ) ነገረቻቸው። ሁለቱ ደቀ መዛሙርትም የሆነውን ሄደው አዩ እውነትም ጌታ መቃብር ውስጥ አልነበረም።
ነገር ግን ጌታ ከሙታን እንደሚነሳ የተነገረውን የመጽሐፍ ቃል ገና አላስተዋሉም ነበር።

"ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፥ ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም።"

መዝሙረ ዳዊት 16 : 10

በወቅቱ ደቀ መዛሙርቱ ቢረበሹ እና ቢደናገጡም ግን ኢየሱስ ስለሀጢአታችን የሞተ እና ሞትን ያሸነፈ ጀግና ነው።

"ስለዚህ የሕዝብን ኃጢአት ለማስተስረይ፥ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን፥ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው።"

ወደ ዕብራውያን 2 : 17

ሊቀ ካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ሰው ሆኖ መጥቶ ለሰው ልጆች የዘላለምን ህይወት ሊሰጥ እርሱ ሞተ። ሞታችንን ሞቶ በትን ሳኤው ሕይወት ሰጠን።

"በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።"

የዮሐንስ ወንጌል 3 : 16




እግዚአብሔር ይባርካችሁ!!!
Telegram post media የኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይና ስቅለት!

የዮሐንስ ወንጌል 19
(ይህንን ክፍል ከመጽሐፍ ቅዱስ አንብቡት)

ኢየሱስ ለፍርድ ከቀረበ በኋላ ወደ ተለያዩ ሹማምንት ወስደውት በመጨረሻ ወደ ጲላጦስ ወሰዱት። ጲላጦስ ኢየሱስ ላይ ጥፋት ስላላገኘበት አስገርፎ ብቻ ሊለቀው ቢያስብም ህዝቡ ግን እንዲሰቀል ጫና ስላሳደሩበት ባይዋጥለትም ግን እንዲሰቀል ፈረደ። ብዙ ካሰቃዩትና ከገረፉት በኋላ በሁለት ወንበዴዎች መካከል ሰቀሉት።

ምንም ኃጢአት የሌለበት ኢየሱስ ስለ እኛ ሀጢአት ስርየት በመስቀል ተሰቅሎ ደሙን አፈሰሰልን፣ ህመማችንን ታመመ። ስለእኛ ሞቶ በሞቱ ህይወት ሰጠን።

"እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።"

ትንቢተ ኢሳይያስ 53 : 5


የተከፈለልንን ዋጋ እለት እለት እያሰብን እግዚአብሔርን እናመስግን። ኢየሱስ ይወዳችኋል በእርሱ በማመን በእረፍት ኑሩ።

እግዚአብሔር ይባርካችሁ!!!
Telegram post media የኢየሱስ ለፍርድ መቅረብና የጴጥሮስ ክህደት!

የዮሐንስ ወንጌል 18 13 - 40
(ይህንን ክፍል ከመጽሐፍ ቅዱስ አንብቡት)

እንግዲህ ኢየሱስ ተላልፍ ከተሰጠ በኋላ እንደየደረጃቸው የተለያዩ አመራሮች ጋር ለፍርድ ቀረበ። መጀመሪያ ሊቀ ካህናቱ ሀና እና ቀያፋ የሚባሉት ዘንድ ቀረበ በመቀጠል ሔሮድስ ጋር ወሰዱት ከዚያ በመጨረሻ ጲላጦስ ጋር አቀረቡት። ወቅቱ እስራኤላውያን ከግብፅ የወጡበትን ቀን በማስታወስ በየአመቱ የሚያከብሩት የፋሲካ (የመውጣት) በዓል ነበር። እንግዲህ በዚህ ወቅት ደግሞ አንድ እስረኛ ጲላጦስ የመፍታት ልማድ ነበረው። በዚህ አጋጣሚ ምንም ስላላጠፋ ኢየሱስን ሊለቀው እንደሚችል ሲነግራቸው ለሸንጎ ያቀረቡት ካህናት እና ህዝቡ በመቃወም ወንበዴ የነበረው በርባን የተባለው ሰው እንዲፈታ እና ኢየሱስ ግን እንዲፈረድበት ጮሁ። ጲላጦስም እንደፈቃዳቸው አደረገ።

በተያያዘ መልኩ ኢየሱስ ሲያዝ ደቀ መዛሙርቱ ቢበታተኑም ጴጥሮስ የተባለው ደቀ መዝሙር ግን ሁኔታውን ለመየት ይከተለው ነበር። በመሀል ያዩት ሰዎች እርሱ ከኢየሱስ ጋር እንደነበር ሲጠይቁት አላውቀውም ብሎ ዶሮ ከመጮሁ በፊት ሶስት ጊዜ ካደ። በእርግጥ መጨረሻ ላይ ንሰሀ ገብቶ ዳግም ኢየሱስን ተከተለው።

ኢየሱስ በዚህ ሁሉ መንገድ የሔደው ጥፋት ስላለበት ሳይሆን እኛን ለማዳን እና ከእግዚአብሔር ጋር ሰዎችን ለማስታረቅ ነው።

"እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ።"

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5 : 19


እግዚአብሔር ይባርካችሁ!!!
Telegram post media ኢየሱስ ተላልፎ ተሰጠ!

የዮሐንስ ወንጌል 18:1 -12
(ይህንን ክፍል ከመጽሐፍ ቅዱስ አንብቡት)

ጌታችን እና መድሀኒታችን ኢየሱስ ቀደም ብለን የተመለከትነውን ፀሎት ከፀለየ በኋላ ከቄድሮን ወንዝ ማዶ ከሚገኝ የአትክልት ስፍራ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ሔደ። ኢየሱስን አሳልፎ ሊሰጥ ከካህናት አለቆች እና ፃሕፍት ጋር በ 30 ዲናር የተስማማው የአስቆሮቱ ይሁዳ የሔዱበትን ቦታ ያውቅ ስለነበር ኢየሱስን ሊይዙ የተዘጋጁትን ጭፍሮች አስከትሎ ወደ አትክልት ስፍራው ሔደ።
ኢየሱስ ተዘጋጅቶ ስለነበር የመጡት ጭፍሮች ማንን እንደሚፈልጉ ጠየቃቸው። እነርሱም የናዝሬቱ ኢየሱስን እንደሚፈልጉ ሲነግሩት እሱ እንደሆነ ሲገልፅላቸው በመጀመሪያ አፈግፍገው ወደ ኋላቸው ወደቁ። ድጋሚ ከተነጋገሩ በኋላ እሱን የሚፈልጉ ከሆነ እንዲወስዱት ነገር ግን አብረውት የነበሩትን ደቀ መዛሙርት እንዳይነኳቸው ነገራቸው።
የመጡት ጭፍሮችም ኢየሱስን ይዘው ወደ ፍርድ ቦታ ወሰዱት።

ኢየሱስ ሊይዙት የመጡትን የማስቆም አቅም ቢኖረውም ግን የመጣበትን አላማ ለመፈፀም እንደ ወንበዴ ሊይዙት ሲመጡ ጊዜው ደርሶ ስለነበር አልተቃወማቸውም። ይህንን ያደረገው በደለኛ ስለሆነ ሳይሆን ስለእኛ በደልና መተላለፍ ነው።

ኢየሱስ ሁላችንንም ይወደናል!!!

እግዚአብሔር ይባርካችሁ!!!
Telegram post media የኢየሱስ ፀሎት!

የዮሐንስ ወንጌልምዕራፍ 17
(ሀሳቡ ሙሉ እንዲሆን ምዕራፍ 16 እና 17 ሙሉውን አንብቡት)

እዚህ ክፍል ላይ ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣበትን አላማ ለመፈፀም በተቃረበበት ወቅት ደቀ መዛሙርቱ ሊያውቁት ስለሚገባው ነገር እንዲሁም ከእሱ በኋላ ስለሚመጣው መንፈስ ቅዱስ እርሱም አሁን ቢነግራቸው ሊረዱት ስለማይችሉት ነገር መንፈስ ቅዱስ ሲመጣ እንደሚያስረዳቸው ከነገራቸው በኋላ ወደ አባቱ ወደ እግዚአብሔር ሲፀልይ እንመለከታለን። ስለተቀበሉት ሁሉ እንዲሁም በእርሱ ስላመኑት ጭምር ጥበቃ እና ከለላ እንዲበዛላቸው ወደ አባቱ ፀለየ። የእርሱ የሆኑት ሁሉ የእግዚአብሔር አብ እንደሆኑማረጋገጫ ሰጠ።

"የእኔም የሆነ ሁሉ የአንተ ነው የአንተውም የእኔ ነው፤ እኔም ስለ እነርሱ ከብሬአለሁ።"

የዮሐንስ ወንጌል 17 : 10

ዛሬም በክርስቶስ ኢየሱስ ለምናምን ከእግዚአብሔር ዘንድ ዋስትና አለን እና ደስ ይበለን። አሁንም መንፈስ ቅዱስ ከፈቀድንለት በሕይወታችን ይሰራል።

መፅሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ እስከመጨረሻው እንደወደደን ማረጋገጫ ይሰጠናል።

"ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ አውቆ፥ በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው።"

የዮሐንስ ወንጌል 13 : 1


እግዚአብሔር ይባርካችሁ!!!
Telegram post media መንፈስ ቅዱስ ወደ እውነት ሁሉ የሚመራ መንፈስ ነው!

"ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።"

የዮሐንስ ወንጌል 16 : 13

ከዚህ በፊት ባየነው ክፍል ኢየሱስ ምድር ላይ የመጣበትን ተልዕኮ ከፈፀመ በኋላ ወደ አብ ሲሄድ መንፈስ ቅዱስን ለዘላለም ከእኛ ጋር እንዲኖር እንደሚልከው ቃል በገባው መሰረት አሁን ላይ ይህ የጌታ መንፈስ በመካከላችን ይሰራል።

እግዚአብሔር የፈቃድ አምላክ ስለሆነ በግድ ሳይሆን እኛ በፈቀድንለት መጠን በእኛ ሊኖር እና ሊሰራ ይወዳል። መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን እንዲሰራ እድሉን ከሰጠነው ሊያግዘን እና ወደ እውነት ሊመራን ዝግጁ ነው። በኢየሱስ በኩል ባገኘነው ቤዛነት በኩል የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ ስልጣን ተሰጥቶናል። ይህንን እድል ግን ምናገኘው ኢየሱስን እንደ ግል አዳኝ ተቀብለን ዳግም ስንወለድ ነው።

"ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤"

የዮሐንስ ወንጌል 1 : 12


ዳግም መወለድ ማለት ድጋሚ ወደ እናታችን ማህፀን መመለስ ሳይሆን ድህነትን በማግኘት በውሀ ጥምቀት እና በመንፈስ ቅዱስ ሙላት ነው። ሰው ደግሞ ዳግም ካልተወለደ በስተቀር ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊመጣ አይችልም። ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት ብቸኛ መንገድ ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

"ኢየሱስም። እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።"

የዮሐንስ ወንጌል 14 : 6

የኢየሱስን አዳኝነት የሚያኮስስ የትኛውም ትምህርት ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። ይህንን እውነት ከተረዳን ኢየሱስን በመቀበል ወደ እውነት የሚመራንን መንፈስ ቅዱስን ወደ ህይወታችን እንዲገባ እና እንዲሰራ እንፍቀድለት። ኢየሱስ ሁላችሁንም ይወዳችኋል።


እግዚአብሔር ይባርካችሁ!!!
Telegram post media ኢየሱስ እንደወደደን እርስ በእርሳችን እንዋደድ!

"እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት።"

የዮሐንስ ወንጌል 15 : 12


ኢየሱስ ወደዚህ ምድር ስጋ ለብሶ እና ከአምላክነት ክብሩ ዝቅ ብሎ የተገለጠው ከእኛ የሚያገኘው ጥቅም ስላለው ሳይሆን እንዲሁ ስለወደደን ነው። በሰራነው ኃጢአት እና በደል ምክንያት እንደ ሙታን ስንቆጠር እርሱ ግን ስለወደደን እና ስለራራልን በደላችንን ሊሸከም ህመማችንን ሊታመም ወደ ምድር መጣ። ከሀጢአት ውጪ ሰው በሚፈተንበት ፈተና ሁሉ ተፈትኗል።

"ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም።"

ወደ ዕብራውያን 4 : 15

በዚህ ሁሉ ግን ኢየሱስ ለእኛ ያለው ፍቅር ፍፁም ነው። እኛም ልክ እንደሱ ሰውን ሁሉ እንድንወድ ይፈልጋል። እግዚአብሔር እንድናደርግ የሚፈልገው ትልቁ ነገር እርስ በእርስ እንድንዋደድ ነው።


"ማንም። እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?"

1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4 : 20



እስኪ ውስጣችንን እንፈትሽ። የምንጠላው ወይም የተቀየምነው ሰው ይኖር ይሆን? ዛሬውኑ ይቅር ማለት ያለብንን ይቅር እንበል፣ ይቅርታ መጠየቅ ያለብንን እንጠይቅ። ይቅር ማለት ካቃተን እንኳን እግዚአብሔር ልባችንን እንዲያራራው እንፀልይ።


እግዚአብሔር ይባርካችሁ!!!
Telegram post media ከኢየሱስ ጋር መሆን ፍሬያማ ያደርጋል!

የዮሐንስ ወንጌል 15:1-8
(ይህን ክፍል ከመጽሐፍ ቅዱስ እናንብብ)

እዚህ ክፍል ላይ ኢየሱስ ሲናገር የእሱ እና የምዕመናኑን ግንኙነት ሊኖረው የሚገባውን መልክ በወይን ተክል ግንድ እና ቅርንጫፍ መካከል እንዳለው አይነት መስተጋብር ሊሆን እንደሚገባው በምሳሌ ያስረዳል።

"እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ ገበሬውም አባቴ ነው።"

የዮሐንስ ወንጌል 15 : 1

በተፈጥሮ ህግ ውስጥ የአትክልት ቅርንጫፍ የሚደርቀው በግንዱ አማካኝነት ከስሩ የሚመጣለትን ውሀ እና ንጥረ ነገር በአግባቡ ካልተመገበ ነው።ልክ እንደዚሁ ደግሞ ሰውም ከኢየሱስ ካልተማረ በሕይወቱ ውስጥ የመንፈሳዊ ድርቀት ያጋጥመዋል።

ከኢየሱስ ለመማር የሚረዳን አንዱ መጽሐፍ ቅዱስ ማንብ ሲሆን ሌላው ደግሞ ፀሎት ነው። ሁለቱንም ነገሮች አመጣጥነን ካላዘወተርን ለተሳሳቱ እና ከእግዚአብሔር ላልሆኑ ትምህርቶች እንጋለጣለን። የመንፈሳዊ ድርቀት እንዳይሆንብን አዘውትረን የእግዚአብሔርን ቃል እናንብብ እንዲሁም እንፀልይ። የዚያን ጊዜ እኛ በክርስቶ እርሱም ደግሞ በእኛ ይኖራል።

"እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።"

የዮሐንስ ወንጌል 15 : 5

እግዚአብሔር ይባርካችሁ!!!
Telegram post media መንፈስ ቅዱስ!!!

" ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤
እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።"

የዮሐንስ ወንጌል 14 : 15 - 17

ኢየሱስ ምድር ላይ ያለው ቆይታ ማብቂያው ሲቃረብ የተለያየ ተስፋ ለተከታዮቹ ሲሰጥ እየተመለከትን ነው። እሱ የተናገረው ተስፋ እስኪፈፀም እና መንግስተሰማይ ሔዶ ዳግም ሊወስደን ከመምጣቱ በፊት ብቻችንን እንዳንሆን አፅናኙን መንፈስ (መንፈስ ቅዱስን) እንደሚልክ ቃል ገብቷል። እዚህ ክፍል ላይ እንደሚናገረው ይህንን መንፈስ አለም ሊያየው እና ሊያውቀው እንደማይችል ይናገራል። ይህ ቅዱስ የእግዚአብሔር መንፈስ አሁንም ይሰራል ከምንም ነገር የበለጠ የቅርባችን ነው። ስናዝን ያፅናናል፣ ስንደክም ያበረታናል፣ ግራ ሲገባን መፍትሄ ይሰጠናል፣ ስንደሰት አብሮን ደስ ይለዋል።

"እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤"

ወደ ሮሜ ሰዎች 8 : 26



እግዚአብሔር ይባርካችሁ!!!
Telegram post media ኢየሱስ ወደ አብ (እግዚአብሔር ) የምንቀርብበት ብቸኛ መንገድ ነው!


" ኢየሱስም። እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።"

የዮሐንስ ወንጌል 14 : 6

በዮሐንስ ወንጌል 14:1- 11 ድረስ ያለውን ክፍል በደንብ አንብቡት።

ኢየሱስ በዚህ ምድር ያለው ተልዕኮ እና ቆይታ ሊያበቃ እንደሆነ ስለሚያውቅ ተከታዮቹን እና ደቀመዛሙርቱን ሲያበረታ እናያለን። ልባቸው እንዳይታወክ በእግዚአብሔር እና በእሱ እንዲያምኑ ይናገራል። በእግዚአብሔር ቤት (እግዚአብሔር በሚነኝበት ስፍራ) ብዙ መኖሪያ እንዳለ እና በዚያ ስፍራ እንደሚያዘጋጅ ይነግራቸዋል። ከደቀ መዛሙርቱ መካከል ቶማስ የተባለው ወዴት እንደሚሄድ እንደማያውቁ እና እንዴት ማወቅ እንደሚችሉ ይጠይቀዋል። በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እሱ እራሱ መንገድ እንደሆነ እንዲሁም ወደ እግዚአብሔር መድረሻ ብቸኛ መንገድ እንደሆነ ነገረው። ፊሊጶስ የተባለው ደቀ መዝሙር አብን እንዲያሳያቸው ሲጠይቅ አብን ለማወቅ ኢየሱስን ማወቅ በቂ እንደሆነ እና እሱን ያየ አብን እንዳየ እንደሚቆጠር ነገረው።

"እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ ስለ ራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ።"

የዮሐንስ ወንጌል 14 : 11

እንግዲህ ከዚህ ክፍል እንደተረዳነው ብቸኛ የመዳን መንገድ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በእሱ በማመን ስላገኘነው በረከት ደስ ይበለን። እሱን ለማመን እያመነታን ከሆነ ደግሞ የመዳን ቀን አሁን ነው። ስለ ነገ እርግጠኛ አይደለንም ዛሬውኑ ወስነን ኢየሱስን እንከተል። ኢየሱስ ሁሉንም ሰው ይወዳል።

እግዚአብሔር ይባርካችሁ!!!
Telegram Channel Link information
Country 🌐 International
Language English
Type Telegram Channel Link
Subscribers 219
Rate this group

How would you rate this community?

0.0 ★ Join Group →