Home › Groups › AAU-Official
AAU-Official Telegram
Telegram Channel Link

AAU-Official Telegram Channel Link

★★★★★ 0.0 (0 ratings)
👁 1 views ↗ 0 joins
🌐 International 🌐 English # General
About this telegram channel link
Addis Ababa University
Telegram Channel

Latest public posts from this Telegram channel.

247 subscribers
30 Oct 2026 latest post
Click to fetch the latest posts directly from Telegram.
Telegram post media AAU Connect | Volume XIX | September 2026

Continental Recognition!

Edition XIX celebrates AAU’s Mastercard Foundation AHEFT Prize recognition and looks ahead to the opportunities it brings for strengthening clinical excellence.

Also, inside are the President’s message as we welcome the new academic year, exploration of AAU’s vibrant activities, and spotlight of its distinguished alumni, community-oriented research and strong partnerships.

Join us in celebrating our University community’s achievements and aspirations.

Read and share “Continental Recognition” here

https://volume.aau.edu.et/2,3d9ea044a47e5d
Telegram post media ያገር መዓዛ ምሽት!
አንጋፋ የኪነጥበብ ምሽት!


የ62ኛ ምሽት እንግዳችን፤ በኢትዮጵያ የሬዲዮ ጋዜጠኝነት ታሪክ ውስጥ የማይፋቅ አሻራዋን ያኖረች፤ በቃል ጥበቧ ትውልድን ያነጋገረች፤ የሰዎችን የሕይወት ታሪክ በጥበብ የምትፈታ፤ አንጋፋዋ የሚዲያ ባለሟል መዓዛ ብሩ ናት!

ያገር መዓዛ ምሽት!

ለዓመታት ብዙ ሺዎችን ስታነጋግር፣ የታሪክ ጓዳቸውን ስትበረብር፤ የሕይወት መንገዳቸውን ስትፈትሽ የኖረችው ልሳነ-ርቱዋ መዓዛ ብሩ በዚህ ታሪካዊ ምሽት የእርሷን የራሷን ታሪክ ታወጋናለች! ጠያቂዋ ትጠየቃለች! እንግዳ አክባሪዋ ትከበራለች!

ከሕይወት ጉዞዋ፤ ከሙያዊ ፍልስፍናዋ፤ ከ"ጨዋታ" እስከ "ሸገር" ተረማምዳ ካለፈቻቸውና ካሳለፈቻቸው የሚዲያ ሙያዊ ጉዞዋ፤ ከማይረሱ የስቱዲዮ ትዝታዎቿ፤ ከድልና ከፈተና የሕይወት አጋጣሚዎቿ ያለስስት ጠልቀን እየቀዳን እንጎነጭ ዘንድ ልቧን፣ አእምሮዋን፣ መንፈሷን፣...ግልጽ አድርጋ በልዩ እመቤታዊ ትህትና ትቀርብልናለች፡፡ እኛም ከአየር ሞገድ እመቤቲቱ ፍቅር የተሞላበት ደግ ልቧ ጠልቀን በነጻነት እንዋኛለን፡፡ ያለገደብ እናወጋታለን፡፡ በፍቅር እናዳምጣታለን!

የጥበብ ማዕዳችን ሰፊ፤ ገበታችንም ሙሉ ነው! ግጥም፣ ወግ፣ ሙዚቃ፣ ሂስና ዳንስ እንደተለመደው ዓይነት በዓይነት ተዘጋጅተውላችኋል።

📅 ረቡዕ፣ ጥቅምት 17፣ 2019 ዓ.ም.

🕠 11:30 ሰዓት

📍 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል፣ ስድስት ኪሎ ግቢ

አንድ ምሽት፣ ብዙ ታሪኮች!

አንድ መድረክ፣ ሺህ ስሜቶች!

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
Telegram post media 🎬✨ልዩ የአጭር ጊዜ ስልጠና ለምትፈልጉ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ የቴአትር እና ፊልም ጥበባት ት/ቤት
Telegram post media የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ የ10 ምሁራንን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ደረጃ እድገት አፀደቀ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ የ10 ምሁራንን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ደረጃ እድገት አፅድቋል።

እድገቱ ምሁራኑ በትምህርትና አካዳሚያዊ አገልግሎት፣ በምርምር እና በማኅበረሰብ አገልግሎት ያስመዘገቧቸውን የላቀ ውጤቶችና አስተዋፅዖዎች መሠረት ያደረገ ነው።

ወደ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ያደጉት ምሁራን፦

1. ዶ/ር አብርሃም ገብሬ ታረቀኝ - በስትራክቸራል ኢንጂነሪንግ ፕሮፌሰር
2. ዶ/ር አዳነ ቢተው ተገኘ- በሜዲካል ማይክሮባዮሎጂ ፕሮፌሰር
3. ዶ/ር አደይ ፈለቀ ደስታ- በኢንቫይሮሜንታል ማይክሮባዮሎጂ ፕሮፌሰር
4. ዶ/ር ደሳለኝ ያየህ አያል- በዲሳስተር ሪስክ ማኔጂሜንት ፕሮፌሰር
5. ዶ/ር ኃይለልዑል ንጉሴ ዱባለ- በቨተርነሪ ኢፒዲሞሎጂ ፕሮፌሰር
6. ዶ/ር ካሳ ሚካኤል ወ/የሱስ- በማቲማቲክስ ኢጁኬሽን ፕሮፌሰር
7. ዶ/ር ሰለሞን ገነት ገብሬ- በባዮኬሚስትሪ ፕሮፌሰር
8. ዶ/ር ሰለሞን አረዓያ ካሳ- በጀነራል ኢዱኬሽን ፕሮፌሰር
9. ዶ/ር ያረጋል አሳቤ ላቀ- በአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ፕሮፌሰር
10. ዶ/ር የድልፋና ሰጣርጌ መኮንን- በፊዚካል ኬሚስትሪ ፕሮፌሰር

ይህ ስኬት ዩኒቨርሲቲው ለአካዳሚያዊ ልህቀት፣ ለምርምርና ፈጠራ እንዲሁም ለማኅበረሰብ አገልግሎት ያበረከተውንና እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለዚህ ከፍተኛው የአካዳሚክ ማዕረግ ለበቃችሁ ምሁራን እንኳን ደስ አላችሁ እያለ፣ በቀጣይ የጀመርነውን የአካዳሚክ፣ ምርምርና አገልግሎት ልቀት ለማምጣት ከመቼውም በላይ እንደምትተጉ በማመን ነው፡፡
Telegram post media የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስታርታፕ ማዕከል “ሎሚ ዴሊቨሪ” የተሰኘ አዲስ የምግብና የዕለት ተዕለት አገልግሎቶች መተግበሪያን ይፋ አደረገ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተዘጋጀው ይህ የፈጠራ ስራ፤ በአካባቢው ለሚገኙ ተማሪዎች ጥራት ያላቸውን ምግቦች በቀላሉ ተደራሽ ከማድረግ ባለፈ፤ የቁሳቁስ፣ የሰነዶች፣ እና የተለያዩ አቅርቦቶችን በቀጥታ ወደ ተማሪዎች መኝታ ክፍሎች እና ቢሮዎች የማድረስ አቅም አለው።

በማስጀመሪያ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ፤ ይህ ስታርታፕ ዩኒቨርሲቲው ከያዘው አቅጣጫና ግብ አንፃር ወሳኝ መሆኑን አንስተው፣ መተግበሪያው በግቢው ውስጥ ተጀምሮ በቀጣይ አድማሱን በማስፋት ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እንዲሁም ለአካባቢው ማሕበረሰብ ሁለገብ አገልግሎት የሚሰጥበትን አቅጣጫ አመላክተዋል፡፡

መተግበሪያዉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስታርታፕ ማዕከል ድጋፍና ስልጠና የተገነባ ሲሆን፣ በግቢው ውስጥ ለተፈጠሩ የምግብና የአቅርቦት ተደራሽነት ችግሮች በተማሪዎች የተሰጠ ተግባራዊ ምላሽ ነው።

“ሎሚ ዴሊቨሪ” በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ የሙከራ አገልግሎቱን በመጀመር ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መተግበሪያውን በመሞከር ሀሳብ በመስጠት እና የፈጠራ ስራውን በማበረታታት አብሮን እንዲቆም ጥሪ እናቀርባለን። መተግበሪያውን በመጠቀም የትምህርት ቆይታዎን ማቀለል እና ለተማሪዎች የሚደረገውን የሥራ ዕድል ፈጠራ መደገፍ ይችላሉ።

መተግበሪያውን ለመሞከር ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ፡

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.lomidelivery.user

https://apps.apple.com/ae/app/lomi-delivery/id6762377526

Telegram: https://t.me/lomi_delivery
Telegram post media 🎶 የሙዚቃው አበጋዝ ምሽት!

✨ አንጋፋ የኪነጥበብ ምሽት!

በ61ኛው የኪነጥበብ ምሽት እንግዳችን፣አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዮታ ነው!

📅 ረቡዕ፣ ጥቅምት 11፣ 2019 ዓ.ም.
🕠 11:30 ሰዓት
📍 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል፣ ስድስት ኪሎ ግቢ

አንድ ምሽት፣ ብዙ ታሪኮች!
አንድ መድረክ፣ ሺህ ስሜቶች
Telegram post media የአበጋዝን የክብር ምሽት በድምፃቸው የሚያደምቁት እነማን ይሆኑ?

🎶 የሙዚቃው አበጋዝ ምሽት!

✨ አንጋፋ የኪነጥበብ ምሽት!

በ61ኛው የኪነጥበብ ምሽት እንግዳችን፣ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪካዊ ጉዞ ውስጥ የማይፋቅ ወርቃማ አሻራውን ያሳረፈው፣ አንጋፋው የጥበብ ሰው፣ የሙዚቃ ቃና ባለሟሉ አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዮታ ነው!

🎤 ታዲያ በዚህ ልዩ የክብር ምሽት ለአበጋዝ ክብረወርቅ ሺዮታ ክብር የትኞቹ ታዋቂ ድምጻዊያን መድረኩን ይደምቁ ይሆን?

📅 ረቡዕ፣ ጥቅምት 11፣ 2019 ዓ.ም.
🕠 11:30 ሰዓት
📍 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል፣ ስድስት ኪሎ ግቢ

አንድ ምሽት፣ ብዙ ታሪኮች!
አንድ መድረክ፣ ሺህ ስሜቶች!
Telegram post media 🎙 CALL to Join AAU FM 99.4 CLUB

Do you want to make your voice heard?

Are you curious about public speaking, interviewing, research, scriptwriting, media production, and current affairs? Do you want to learn how to identify, verify, and share reliable information?

👉 If yes, this club is for you!

The AAU FM 99.4 CLUB is a new student‑led initiative in collaboration with AAU Community Radio FM 99.4. It’s designed to help students from all backgrounds gain practical communication and media skills while actively engaging in public communication activities.

✅ What You’ll Gain
• Host real radio programs • Certificates of media experience & training • Skills in program production, scriptwriting, interviewing & presentation • Public speaking & communication confidence • Media & digital literacy • Workshops on misinformation & fact‑checking • Knowledge of media law & ethics • Leadership & teamwork opportunities • Friendships & professional networks • CV‑boosting practical experience

👥 Who Can Join? All AAU students — from any department, any year of study.
No prior media experience required. Just bring your interest, commitment, and willingness to learn!

⚠️ Limited Slots Available! Register early to secure your place.

🔗 Registration: https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScB-ODKRNHbfJcW22ZEibpAQ1lhBfdv9o2RVMmNv-rhaMf0hg/viewform?usp=dialog

📅 Registration Deadline: Oct 13, 2026 G.C.

Make Your Voice Heard. Build Your Skills. Join AAU FM 99.4 CLUB!!!
Telegram post media አንጋፋ የኪነጥበብ ምሽት!

የዛሬ ሁለት ሳምንት በ61ኛ ምሽት ወደክብር መድረኩ ይመለሳል!

በቤታችን፣ ኪነጥበብ እንደ ወንዝ ይፈሳል! በ60 ምሽቶች ያሳለፍናቸው ደማቅ ዝግጅቶቻችን አይረሴ ትዝታዎቻችሁ እንደሆኑ እምነታችን ነው፡፡

አሁን ለ61ኛ ጊዜ ሲፈስ፣ ጽዋው በከፍታ የሚነሳለት የክብር እንግዳችን በኢትዮጵያ ሙዚቃ የታሪክ ጉዞ ሂደት ውስጥ ወርቃማ አሻራውን በደማቁ ያተመው፤ አንጋፋው ጠቢብ፤ ታላቁ የሙዚቃ ቃና ባለሟል አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዮታ ነው!

የሙዚቃው አበጋዝ ምሽት!

በዚህ ታሪካዊ ምሽት ታላቁ የሙዚቃ ጥበብ ባለሟል በሦስት ትውልዶች ሕብራዊ ድምጽ ስሙ በክብር ይነሳል! ይመሰገናል!! በሥራዎቹ እየተወደሰ ይዘከራል!!!

ከሕይወት ጉዞው፤ ከሙዚቃ ፍልስፍናው፤ ከፈጠራ ሂደቱ፤ ከመድረክና ከስቱዲዮ ትዝታዎቹ፤ ከዘመን ዘመን የተሻገረ የጥበብ ልምዱን በልዩ አቀራረብ እየዋጀናቸው እናያቸዋለን፤ እንሰማቸዋለን።

የክብር መድረኩ የእርሱ ነው፤ ለክብሩ ዝነኞቹ ድምጻዊያን ይዘፍናሉ።(እነማን ናቸው?..... ምስጢር ነው)

የጥበብ ማዕዳችን ሰፊ፤ ገበታችንም ሙሉ ነው! ግጥም፣ ወግ፣ ሙዚቃ፣ ሂስ፣ ዳንስና ፋሽን ሾው እንደተለመደው አይነት በአይነት ተዘጋጅተውላችኋል፡፡

📅 ረቡዕ፣ ጥቅምት 11፣ 2019 ዓ.ም.

🕠 11:30 ሰዓት

📍 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል፣ ስድስት ኪሎ ግቢ

አንድ ምሽት፣ ብዙ ታሪኮች
አንድ መድረክ፣ ሺ ስሜቶች።

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
Telegram post media 📣 Do you want to learn Sign Language?

The Department of Linguistics and Philology (Ethiopian Sign Language Program Unit) is excited to announce the launch of a Non-Credit Ethiopian Sign Language Course at reasonable fees!

📅 Classes start October 10

🕘 Every Saturday at 9:00 AM

📍 NCR G-16, 15, 14, and 13

👉 Registration available at OCR 423–424.

Open to students and staff, inside and outside AAU
Telegram post media 📢 Chinese Language Certificate Program

✨ Registration Open for New Batch!

🗓 Deadline: Oct. 12, 2026 (Mon–Fri, 9–11 AM)

📍 Registration Office: Forum Building, 8th Floor – Confucius Institute, Sidist Kilo Campus, AAU

🎓 Program Details: • 10‑week Elementary Chinese Certificate

• Classes start Oct. 17, 2026 • Every Saturday, 1–3 PM • Level: 1

⚠️ Seats are limited — registration closes automatically once full!
Telegram post media ⚠️ ATTENTION!

The information currently circulating is NOT AUTHENTIC.

No such announcement has been officially dispatched by the AAU Registrar.

🔵 AAU’s official Telegram channel has a BLUE VERIFICATION MARK.

🚨 Do NOT totally follow or rely on announcements from any other Telegram channels claiming to represent AAU.

❌ Unofficial Channels:

AAUMEREJA — more than 38,000 followers
AAU NEWS — more than 19,000 followers
AAU Info Center — more than 26,000 followers

⚠️ Please be careful and do not follow or rely on other channels for official AAU announcements.

📢 Stay alert. Stay informed.
Telegram post media ⚠️ Attention!!

The above information circulating is not authentic.

No such announcement has been dispatched from the AAU Registrar.

✅ Please rely only on the official AAU Telegram Channel for accurate updates.

ከላይ የተያያዘውን መረጃ የ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ረጅስትራር የማያውቀው መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
Telegram post media AAU CONNECT | VOLUME XVIII | AUGUST 2026

60th Anniversary of the Kennedy Memorial Library

The latest edition of AAU Connect celebrates six decades of the John F. Kennedy Memorial Library and its place in the longstanding partnership between Addis Ababa University and the United States.

Explore this edition also featuring stories on academic excellence, partnerships, alumni, and the University’s continuing journey.

Read Volume XVIII: https://volume.aau.edu.et/4,3d9e4ef82a6808
Telegram Channel Link information
Category General
Country 🌐 International
Language English
Type Telegram Channel Link
Subscribers 247
Rate this group

How would you rate this community?

0.0 ★ Join Group →